התוכניות

התוכניות שלנו

ስለስኳር በሽታ አጭር መግለጫ
ስኳር ብዛት በሽታ ማለት ምንድን ?

በቀላል አገላለጥ ስኳር ብዛት በሽታ ማለት ወደ ሰውነታችን የምናስገባው ምግብ (ጣፋጭነት ያላቸውን ጨምሮ )የተመዛዘነ ውስጣዊ ስምሪት (ውህደት) ሲዛባ የሚከሰት ሕመም ማለት ነው። ይኸውም ኢንሱሊን የተባለው ተፈጥሯዊ መድሃኒት ነክ ፈሳሽ(*ነጥረ ቅመም) በተመጣጠነ መጠንና ሁኔታ ባለመመንጨንቱ ወይም የመነጨው ትክክለኛ ሥራ ላይ ባለመዋሉ ምክንያት ስኳር በደም ውስጥ ሲጠራቀምና ሲጎዳ ማለት

 • የስኳር ብዛት በሽታ ያለባቸው ሰዎች ኢንሱሊን የተባለውን ንጥረ ቅመም ሰውነታቸው በአግባቡ ማምረት/ማመንጨት ወይም መጠቀም ባመቻሉ ነው፡፡ኢንሱሊን ማለት በሰውነታችን ውስጥ የሚገኝና ሰውነታችን እጅግ የሚፈልገው ዓይነተኛ የንጥረ ቅመም አይነት ኢንሱሊን የሚጠቅመን ከምግባችን የምናገኘውን ስኳርንና ሌሎች ምግቦችን ወደ ግሉኮዝ እንዲቀየር የምያስችል ቅመም ነው ፡፡ግሉኮዝ ደግሞ ለሰውነታችን ኋይል በመስጠት የሰውነታችን ውስጣዊ ሥራ እንዲከናወንና እንድንቀሳቀስ፣እንድናስብ፣ ወዘተ የሚያስችል ኋይል ሰጭ ነው ። በስኳር ብዛት ሕመም ተጠቂ ከሆኑት መካከል
  1/3ኛ የሚያህሉት በሽታው እንዳለበቻው አያውቁም፡፡ በደንብ ካልተከታተሉትና እንክብካቤ ካላደረጉለት የስኳር ብዛት በሽታ ዓይነ ስውርነትን፣ የልብ ሕመምን፣የአንጎል ሕመም ን፣የኩላሊት ሕመምና እግርን እስከማጣት አደጋ ያደርሳል። እንዲያውም አእምሮን በመሳት አካላችን እስከመስለልና አስከ ሞት አደጋም ያደርሳል።
  ስኳር ብዛት ያለባቸው ሰዎች የሚመገቡትን ምግብ በመቆጣጠር፣ የደም ስኳር መጠናቸውን በየጊዜው በማወቅ፣ ክኒን/እንክብል መድኋኒታቸውን በመውሰድና እንዳስፈላጊነቱ ኢንሱሊንም በመወጋት እራሳቸውን ይንከባከባሉ፡፡ ስኳር ብዛት ካለብዎት ሕመምዎን ተገተው መንከባከብና መጠበቅ አለብዎት፡፤ የስኳርዎን መጠን በአግባቡ ከተቆጣጠሩ ጤናማ ሆነው ለረጅም ዕድሜ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡የሕክምና መመሪያዎችን በማከበር በንቃት፣ በትጋትና በመልካምባሕሪና ተግባር በሽታችንን መቆጣጠርና ማዳናም እንችላለን።
  የስኳር ብዛት በሽታ ዓይነቶች፦
  ሁለት ዋና የስኳር ብዛት ዓይነቶች አሉ፣ በአጭሩ ለመለጥ እንጅ ሌሎች ዓይነቶችም አሉ።
  ዓይነት 1: የዚህ በሽታ ተጠቂዎች በሽታው ከልጅነታቸው ጀምሮ የሚመጣባቸው ስለሆነ ማስወገድ አይችሉም፡፡ በአካል ውስጣዊ ግጭቶች ምክንያት ሰውነታቸው በቂ ኢንሱሊን ስለማያመንጭ / ሰለማያመርት ኢንሱሊንን በየቀኑ በመርፌ መውሰድ ግድ ይላቸዋል። ሕይወታቸው በኢንሱሊን ላይ ጥገኛ የሆነ ማለት ነው።
  ዓይነት 2: የዚህ በሽታ ተጠቂዎች ደግሞ በአብዛኛው በዕድሜ ትልቆች ሰዎች ናቸው፡፡ የሰውነታቸው ኢንሱሊን አጠቃቀም ያልተስተካከለ ስለሆነ እነዚህ ሰዎች አመጋገባቸውን መቆጣጠር፣ ሕክምናቸውን በትክክልና በትጋት በመውሰድና ተገቢ የአካል ማጠንከሪያ / ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ አለባቸው፡፡የጤናማ አመጋገብን ዘዴ በየጊዜው በመማርና ምግባቸውንና መጠጣቸውን ተስማሚ ማድረግ አለባቸው።
  ለስኳር ብዛት በሽታ የተጋለጡ እነማን ናቸው?
  ሐኪሞች "ዓይነት 1" ከምን እንደሚነሳና ወይም እንዴት እንደሚመጣ ጠንቅቀው ቢያውቁም፣ ለዚህ ዓይነቱ የስኳር ብዛት በሽታ የሚጋለጡት እነማን እንደሆኑ ግን መለየት አይቻልም፡፡ ወላጆች የዚህ ዓይነቱን የስኳር ብዛት በሽታ ምልክቶች በጥንቃቄ ማወቅ አለባቸው፤ ምክንያቱም ልጆቻቸው ላይ ልዩ ስሜትና ምልክት ካዩ ልጆቻቸውን በፍጥነት ወደ ሐኪም መውሰድ እንዲችሉና እንዲያሳክሙ ለማስቻል ነው፡፡
  በ"ዓይነት 2" የስኳር በሽታ በቀላሉ ሊያዙ የሚችሉት፡-
   ዕድሚያቸው 40 ወይም ከዛ በላይ የሆኑ ፤ አንድዳድ ጊዜ ከ 40 ዓመት በታችም ያሉትም ሊሆኑ ይችላሉ
  ስኳር ብዛት በሽታ ያለበት የቅርብ ዘመድ (ወላጅ፣ ወንድም ወይም እህት) ያላችው
   ወፍራም ሆነው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የማይሰሩ፣ በእኛ በኢትዮጵያኖች ላይ ወፍራም ያልሆንትም አልፎ አልፎ ይገጥማቸዋል
   ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት ወይም ኮሌስትሮል ያለባቸው
  በኢትዮጵያ-እስራኤላዊ ማሕበረስባችን ወስጥ ሕመሙ በስፋት እየታየ በመሆኑ ሁላችንም በንቃት መከታታል አለብን።
  ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሽህ የሚቆጠሩ ሰዎቻችን በ"ዓይነት 2" የስኳር ብዛት በሽታ ተጠቂ ሆነዋል። ይህም የሆነበት ምክንያት ብዙ የሥጋና የቅባት ምግብ፣ በብዙ የአልኮልና የጣፋጭ መጠጦች በመጠቀም ስለሚመገቡና የአካል ብቃት/ጥንካሬ እንቅስቃሴ ስለማያዘወትሩ ነው ። በሁሉም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች ሁሉ ጤናማ አመጋገብና አኗኗርን ማወቅ፣ የስኳር ብዛት በሽታን ለመቋቋምና ብሎም ለመከላከል ያስችላል። በእኛ እስራኤል በምንኖር ኢትዮጵያኖች ዘንድ ለስኳር ብዛት በሽታ ችግራችን ዋና ምክንያት ሆኖ የታወቀው ጉዳይ፣ እዚህች ቅድስት አገር ከመጣን ጀምሮ የምንመገበው የምግብ ዓይንቶችና መጠጦች በመለወጡና መጠኑም ከፍ ያለ በመሆኑ፣በጥቂቱ የለመደው ሰውነታችን ይህን ብዛት ያለውን ምግብ ለያዋህደውና ሊጠቀምበት ባለመቻሉ፣ ትርፍ አድርጎ በደማችን እንዲክማችና ወደ በሽታነት እንዲለወጥ በማድረጉ ነው።
  ይህን ሳይንሳዊ መግለጫ በጥሞና ልንረዳውና መፍትሄውን በመፈልግ ልንጠቀምበት ይገባናል።
  የስኳር ብዛት በሽታ ምልክቶች፡-
  "ዓይነት 1" የስኳር በሽታ ያለባቸው ሕፃናት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ምልክቶች ያሳያሉ
  በቀላሉ የማያልፍ የውኋ ጥማት
   ቶሎ ቶሎ ሽንት መሽናት
  ድካምና መዝለፍለፍ
  ከፍተኛ የሆነ ውፍረት ወይም መክሳት
   ማስመለስ ( ማቅለሽለሽና ማስታወክ )
  • ምክንያቱ ያልታወቀለት ሆድ ሕመም
  በአብዛኛው የ"ዓይነት 1 የስኳር ብዛት በሽታ " ተጠቂዎች ስኳር ብዛት እንዳለባቸው የሚታወቀው ከታመሙ በኋላ ስለሆነ፣ወላጆች ምልክቶችን አይተው ወደ ሐኪም የመውሰድ ዋና ሃላፊነት አለባቸው ፡፡ ለዚህም ትምህርትና ንቃት ወሳኝነት አለው።
  የ "ዓይነት 2" የስኳር ብዛት በሽታ ምልክቶች፦
  የማይጠፋ ከፍተኛ የሆነ የውኋ ጥማት
  • ቶሎ ቶሎ ሽንት መሽናት
   ርሃብ ርሃብ ማለትና በልቶ አለመርካት
  ድካም
   ማቅለሽለሽና ማስመለስ/ማስታወክ
   የዓይን መፍዘዝ / በጥራት አለማየት
   የቀላል ቁስሎች ቶሎ አለመዳን
  እነዚህ ምልክቶች በእርስዎ ወይም በሚ ያውቁት ሰው ላይ ከታዩ ሐኪምዎን ያማክሩ፡፡
  ስኳር ብዛት በሽታን በመታከምና በመ ቆጣጠር/በመንከባከብ ሕሙማን እንደማንኛውም ሰው መደበኛ ኑሮን መምራት ይቻላል፣ ነገር ግን ምልክቶቹን ካላወቁና ወይም ቸል ካሉ ከፍተኛና ውስብስብ የጤና ቀውስ ሊያስከትልብዎ ይችላልና በመማርና አስፈላጊዉን በመፈጸም በሽታውን መከላከል እጅግ አስፈላጊ ነው።
  ስለቅድመ ስኳር ብዛት ሕመምተኞች፦
  የስኳር ብዛት በሽታ ጸጥ ያለ ሆኖ ደርጃ በደረጃ እየተባባሰ የሚመጣ በሽታ ነው። ስለሆነም ቅድመ ስኳር ብዛት ሕመምተኞች በብዛት መኖራቸው ይታወቃል። አስቀድመው ተገቢውን ምርመራ ባለማድረጋቸው ወደ መደበኛ ስኳር ብዛት ሕመምተኛነት ይሸጋገራሉ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ከወጣትነት ዕድሜ ጀምሮ በየጊዜው የደም ስኳር መጠንን ተመርምረን ማወቅ ብንችል፣ በሽታውን በእርግጠኛነት መቋቋምና ብሎም ጭራሹን ማስቆም እንድሚቻል የሕክምና ባለሙያዎች ያስተምራሉ። ይኸውም፣ በተመጣጠነ ጤናማ ምግብና መጠጥ፣ በተዘወተረ የአካል ማጠንከሪያ እንቅስቃሴ፣ውፍረትን በመከላከል፣ውጥረትንና ጭንቀትን በመቋቋምና በማስወገድ፣ የመሳሰሉትን አዎንታዊ እርምጃዎች በመውሰድ በሽታውን መከላከል ይቻላል።

השותפים

השותפים שלנו

 • קרן עזריאלי

  קרן עזריאלי

 • משרד הבריאות

  משרד הבריאות

 • הקרן לידידות

  הקרן לידידות

 • משרד הקליטה

  משרד הקליטה

 • שרותי בריאות כללית

  שרותי בריאות כללית

 • לאומית שירותי בריאות

  לאומית שירותי בריאות

 • סאנופי

  סאנופי

 • pfizer

  pfizer

 • הסוכנות היהודית לארץ ישראל

  הסוכנות היהודית לארץ ישראל

 • שתיל

  שתיל

 • אוהלי רחמים

  אוהלי רחמים

 • Kathryn Ames Foundation

  Kathryn Ames Foundation

 • Orion

  Orion

 • The Levin Family

  The Levin Family

 • הרשויות המקומיות

  הרשויות המקומיות

צרו קשר

Please type your full name.
Invalid email address.
Invalid Input
Invalid Input
אתר זה מוגן על ידי reCAPTCHA ו-Google מדיניות הפרטיות וכן תנאים והגבלות חלים.
Handsrtl