קורונה

קורונה

הודעה לציבור

הממשלה אישרה תקנות לשעת חירום המעגנות את הנחיות משרד הבריאות במטרה ליצור "ריחוק חברתי" כחלק מאסטרטגיית ההתמודדות עם נגיף הקורונה החדש.

20.03.2020
ለሕብረተሰቡ የተሰጠ ማስታዎቂያ
አዲሱን የኮሮና ቫይረስ መዛመት ለማቆም ሲባል ፤ የእስራኤል መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን አጽድቋል ፤ በዚህ አዋጅ ዋና አላማውም የጤና ጥበቃ መ/ቤት የተሰጠውን ሃላፊነት በመጠቀም " ሕብረተሰቡን ማራቅ " የሚለውን መመሪያ ሥራ ላይ ያውላል ።
ይን መመሪያ ዋና አላማው በእስራኤል ሃገር ውስጥ የሕብረተሰቡ ግንኙነት እንዲቀንስ የሚል ነው ። ከጤና ጥበቃ መ/ቤት ባለሙያዎች የተሰጡትን ሃሳቦች የተመረኮዘ ሲሆን ይህን አዲስ በሽታ ባለው የበሽታ ልዩነትና ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ የመተላለፍ ሃይሉ ከፍተኛ ስለሆነ የእስራኤል ሃገር ያላት አማራጭ ይህን አዲስ መመሪያ ስራ ላይ ማዋል ይሆናል ። በሽታው ካንዱ ወደ አንዱ በቶሎ የመዘዋወር ጸባይ ስላለው በዚህ በሽታ ምክንያት ብዛት ያላቸው ሰዎች ይሞታሉ የሚል ግምት ስላለ ይህንን መመሪያ ወይን አዋጅ በተግባር ላይ ማዋል ግድ ይሆናል ።
የተዛዝ መመሪያው እንደሚለው ከሆነ አንድ ሰው ከሌላኛው ሰው ጋር ያለውን አካላዊ ግንኙነት መቀነስ ነው ፤ ግንኙነት ማድረግ ካስፈለገን ደግሞ በጣም አስፈላጊና አንገብጋቢ ለሆኑ ጉዳዮች ብቻ ሲሆን በዚህ መመሪያ መርሆ ሕብረተሰቡ ከተመራ ፤ የበሽታውን የመስፋፋት ዕድል በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል ። ሌላው የመመሪያ መርሆ ደግሞ ፤ ማሕበረሰቡ በሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች ምን ማድረግ እንዳለብን መርሆው ያሳያል ፤ ይህም የሚሆነው አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር ግንኙነት እንዳያደርግና በዚህ መሰረት የበሽታውን መስፋፋት ለማቆም ነው ።

ከላይ የተገለጸውን በመመርኮዝ ፤ የዚህ መመሪያ እንደሚገለጸው ፤ ከቤታችን ወደ ማሕበረሰቡ የመሰብሰቢያ ቦታዎች መቸ መውጣት እንደምንችላ ተእዛዝም ይሰጣል ፤

1. ወደ ሥራ ቦታ መሄድና መመለስ ፤ ይህም የሚሆነው ስለ ሥራ ቦታ ለብቻው በተላለፈው ተእዛዝ መሰረት ነው ፤
2. የተለያዩ ቁሳቁሶችንና ምግብ ለመግዛት ፤ መደኃኒቶችን ለመግዛት ፤ የተለያዩ እስፈላጊና መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ለመግዛት ፤
3. የሕክምና አገልግሎት ለመቀበል ፤
4. የደም ልገሳ ለማድረግ ፤
5. የሰልፍ አድማ ለማድረግ፤

6. የፍርድ ቤት ሂደቶችን ለማስፈጸም ፤
7. በብቸኝነት የስፖርት እንቅስቃሴ ለማድረግ ፤ የአንድ ቤተሰብ አባሎችን ያጠቃለለ ይሆናል ፤
8. የአንድ ሰውና የአንድ ቤተሰብ አካል የሆኑ ሰዎችና አብረው የሚኖሩ ከሆነ ደግሞ ፤ ከመኖሪያ ቤታቸው በመውጣት ወደ ቅርብ የሆነ ቦታ ለትንሽ ጊዜ ሄደው መመለስ ይችላሉ ፤
9. ወደ ተለያዩ የሓይማኖታዊ ስነ-ስርአቶች ፤ ወደ ሠርግና ወደ ቀብር ስነ-ስርአት መሄድ የሚቻለው 10 ሰው በመሆንማ ሁሉም የ 2 ሜት እርቀት በመጠበቅ ነው ፤
10. የሕክምና ወይንም ሌና ከባድ የሆነ ነገር ያጋጠመውን ሰው እርዳታ ለመስጠት ፤
11. ለተለያዩ አስፈላጊ ነገሮች መውጣት ይቻላል ፤

በተጨማሪም የሕዝብ መነሃሪያ ስለሆኑ ቦታዎችም " ከሰው መራቅ " የሚለውም መርሆ ተእዛዝ ላማክበርና የበሽታውን መዛመት ለማቋረጥ የተለያዩ መመሪያዎች ተሰጥተዋል ፤ እነዚህ መመሪያዎችም የሚያጠቃልሉት ፤

12 . በተቻለ መጠ አንዱ ሰው ከሌላኛው ስው የ 2 ሜትር ዕርቀትን መጠበቅ ፤
13 . ከሁለት ሰው ያልበለጠ ተሳፋሪዎችን በመያዝ በግል መኪናዎች መንቀሳቀስ ፤ ይህ ትእዛዝ አንድ
የሆኑ የቤተሰብ አባልንና ለአስፈላጊ ድርጊቶች የሚደረጉን ጉዞዎችና ከሁለት ሰው በላይ
ተጓዦች የሚያስፈልግ ከሆን ይህ መመሪያ እነዚህን ሁኔታዎች አያጠቃልልም ፤
14 . ማንኛውም ለሕብረተሰቡ አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች በሙሉ ፤ ይህ ትእዛዝ እንደሚወስነው ከሆነ
፤ በተላላኪ የምናስመጣቸው ቁሳቁሶች ካሉ ፤ ተላላኪው ያመጣቸውን ቁሳቁሶች ከበሩ ላይ
ወይንም ከበሩ አጠገብ አስቀምጦ መሄድ አለበት ፤ በተጨማሪም ለቤት በጣም አስፈላጊ የሆኑ
ጥገናዎችንም ማስጠገን ይቻላል ።

ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ቦታዎች የመገበያየትና የተለያዩ የመዝናኛ ሂደቶችን መፈጸም ተከልክሏል ፤
1. ትልልቅ የመገበያያ ቦታዎች ( ኬኒዮኒም ) በተጨማሪም የመገበያያ ቦታ ሆኖ በውስጡ ከ 10 በላይ ሱቆችን ያጠቃለለ ወይንም የቦታው መሬት ቆዳ ስፈቱ ከ 3000 ሜት የሚበልጥ ከሆነ እነዚህ ቦታዎች ዝግ መሆን አለባቸው ፤ ይህ መመሪያ የማያጠቃልላቸው ቦታዎች ደግሞ ፤ ምግብ የሚሸጥባቸው ቦታዎች ፤ የመድኃኒት መሸጫ ፋርማሲዎች ፤ ወይንም የተለያዩ የንጽህና ቅባቶችና ምርቶችን የሚሸጡ ሱቆች ነው ፤ ሆኖም ግን የተለያዩ የሱቅ ቦታዎችና ከላያቸው አንድ የጋራ ጣራ የሌላቸውና በአንድ የመሸጫ ቦታ ከ 10 በላይ ሱቆች የሌለባቸው ቦታዎች ፤ ከዚህ በታች በዓንቀጽ (2) ያልተካተቱ ፤ ሱቆች ስራቸውን መስራት መቀጠል ይችላሉ ፤

2. የመዝፈኛ ቤቶች (ዲስኮቴኪም) የመጠጥ ቤቶች ፤ የድግስ ቦታ አዳራሾች ፤ የስፖርት መስሪያ ቦታዎች ፤ የመዋኛ ገንዳዎች ፤ የመዝናኛ የውሃ ቦታዎች ፤ የእንሰሳት መሰባሰቢያ አጥር ግቢዎች ፤ የመታጠቢያ ቦታዎች ፤ የፊልም ማያ አዳራሾች ፤ የቲዓትር ማያ ቦታዎች ፤ የመጫወቻ ማዕከሎች ፤ ሕክምና ያልሆነ የአካል እንክብካቤ የሚሰጡ ቦታዎች ፤ የተለያዮ የድራማና የኢግዚብሽን ማቅረቢያ ቦታዎች ፤ የተለያዩ የማሕበረሰቡ መናኸሪያ የሆኑ ቦታዎች ፤ ከቦታ ወደ ቦታ በዓየር በመንሳፈፊያ የሚንቀሳቀሱ (ራክቫል) ፤ ሙዚየሞች ፤ የተለያዩ የደን ጉብኝቶች ፤ የመጸሃፍት መደብሮች ፤ የተለያዩ የባህልና የጉብኝት ቦታዎች ።

ከዚህም በተጨማሪ ፤ በመመሪያው ትዕዛዝ መሰረትና የተወሰነውን ቅድመ ማሟያ የሚያካትቱ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎች የሚደረጉባቸው ቦታዎችም ተውስነዋል ፤ የሆቴል ቤቶችን ምግብ ቤት ያካተተ ተለያዩ የምግብ ቤቶች ፤ የተለያዩ የምግብ መሸጫ ቦታዎችን ፤ የመድኃኒት መሸጭ መደብሮች (ፋርማሲዎች) እና የተለያዩ የአካል እንክብካቤንና ንጽህናን የሚጠብቁ ቁሳቁሶችን የሚሸጡ ቦታዎች ፤ ከተዘረዘሩ ዓንቀጽ (ለ)(2) ያልተካተቱ የቁሳቁስ መሸጫ ሱቆችን ያጠቃልላል ።

ይህ የትዕዛዝ መመሪያ ለ 7 ቀናት የሚቆይ ነው ፤ ከዚያ በውሃላ ማራዘም ወይንም መቀየር የሚያስፈልግ ከሆኔ ሁኔታውን በመገምገም አዲስ ውሳኔ ይሰጣል ።

השותפים

השותפים שלנו

 • קרן עזריאלי

  קרן עזריאלי

 • משרד הבריאות

  משרד הבריאות

 • הקרן לידידות

  הקרן לידידות

 • משרד הקליטה

  משרד הקליטה

 • שרותי בריאות כללית

  שרותי בריאות כללית

 • לאומית שירותי בריאות

  לאומית שירותי בריאות

 • סאנופי

  סאנופי

 • pfizer

  pfizer

 • הסוכנות היהודית לארץ ישראל

  הסוכנות היהודית לארץ ישראל

 • שתיל

  שתיל

 • אוהלי רחמים

  אוהלי רחמים

 • Kathryn Ames Foundation

  Kathryn Ames Foundation

 • Orion

  Orion

 • The Levin Family

  The Levin Family

 • הרשויות המקומיות

  הרשויות המקומיות

צרו קשר

Please type your full name.
Invalid email address.
Invalid Input
Invalid Input
אתר זה מוגן על ידי reCAPTCHA ו-Google מדיניות הפרטיות וכן תנאים והגבלות חלים.
Handsrtl