קורונה

קורונה

1 / በበሽታው ከተበከሉ ሐገሮች ወደ እስራኤል የሚገባ ሁሉ ለ14 ቀናት ከቤቱ ተገልሎ
እንዲቀመጥ፤
2 / ከእነዚህ አገሮች ወደ እስራኤል የሚገቡ ሌሎች እንግዶች መግባት ይችላሉ ፤ ነገር ግን ለ14
ቀናት ስለመገለላቸው ማረጋገጫ ከተገኘ ብቻ ነው ፤
3 / በአጠቃላይ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች በእስራኤል ውስጥ እንዳይካሄዱ ተወስኗል ፤
4 / ከዓለም አቀፍ ጉባኤዎች የሚመለሱ እስራኤላዊያን ለ14 ቀናት በቤታቸው እንዲገለሉ ፤
5 / የጤና ጥበቃ ሚ/ር ሠራተኞች ወደ ዉጭ አገር እንዳይወጡ ተከልክሏል ፤
6 / ከ 5000 ሰዎች በላይ የሚያስተናግዱ ጉባኤዎች እንዳይካሄዱ ተከልክሏል ፤
7 / ባለፉት 14 ቀኖች ወደ እስራኤል የገቡ ሁሉ፣ 100 ሰዎች በሚሳተፉበት ድግስም ሆነ
ስብሰባ ላይ እንዳይሳተፉ ተከልክሏል 
8 / ለእስራኤል የሠራተኛ ኮሚሽን ከጤና ጥበቃ ሚ/ር በተሰጠው ምክር መሠረት፣
በአጠቃላይ ሠራተኞች ወደ ዉጭ አገራት እንዳይወጡ በማለት ተነግሯል ፤
9 / ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ ላሉና በተለይም ስር ሰደድ በሽታዎች ላሉባቸው ( የስኳር
ብዛት በሽታ ፤ የከፍተኛ የደም ግፊት ፤ የልብና የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችና የተፈጥሮ
የመከላከያ ኋይላቸው ደካማ የሆኑ ሰዎች ለበሽታው ይበለጥ ተጋላጮች በመሆናቸው፣
ሕዝባዊ ስብሰባዎች ፤ ከውጭ አገር ከተመለሱ ሰዎችና የሕመም ስሜት ካላቸው ሰዎች
ጋር ግንኙነት እንዳያደርጉ ተመክሯል ፤
10 / አገር ጎብኝዎች ማለት ከኢራን ፤ ከሱሪያ ፤ ከኢራቅ ፤ ከሊባኖስ ወ.ዘ.ተ ከ14 ቀናት በፊት
ለተመለሱ ወደ እስራኤል እንዳይገቡ ተደርጓል ፤
11 / ጤና ጥበቃ ሚ/ር በጥብቅ የመከረው የግል ንጽህና አጠባበቅና አፈጻጸም ጉዳይ በእጥፍ
ድርብ ትኩረት እንዲደረግበት በማለት ነው ፤
ማሳሰቢያ፦ በአንድ ወቅት የተላለፈ መመሪያ የመጀመሪያም የመጨረሻም ሊሆን
አይችልም። እንደወረርሽኙ የመዛመት ጠባይ፣እንዲሁም እንደ ማሕበራዊና
ኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ሁኔታ እየተጠናና እየተገመገመ፣ መመሪያዎች
ስለሚወጡ፣ በየቀኑ የሚገለጠውን መረጃ ነቅቶ በመከታተል እራስን መጠበቅ
ያስፈልጋል።
ስለ በሽታው ክትባትና መድኋኒት ጉዳይ በተመለከተ
እስከ አሁን ድረስ ለኮሮና ቫይረስ የሕክምና መድኋኒትም ሆነ የመከላከያ ክትባት ገና
አልተገኘለትም ። ይህን ለማግኘት በሚደረገው ጥረት እስራኤልን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ
ከፍ ያለ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ።
ክትባትና መድኋኒትን ለመፍጠር ብዙ ጊዜና ሂደትን የሚጠይቅ በመሆኑ ፤ ለአሁኑ አጣዳፊ
ፍላጎት በቀላሉ ይገኛል ብሎ መገመት ጥቂት ይከብዳል ። ስለዚህ እስከዚያ ድረስ ዋናው
ተጨባጭ እርምጃ ከዚህ በላይ የተገለጡትን የመከላከያ ዘዴዎች በጽኑ ትኩረት መፈጸም ብቻ
ነው ።
" ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ " የተባለውን የሕዝብ ጤና አጠባበቅ መርሆ ከዚህ
ጋር መጥቀስ እጅግ ተገቢና ወቅታዊም ነው ።
* የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ፦ ዶ/ር ሰፈፈ በላይ አይቸህ
በጤና አጠባበቅና በኤፒደሚዎሎጅ መስክ ኤክስፕርት
በጤና ብሪኡት የጤና አጠባበቅ ድርጅት ፕሮፌሽናል ሥራ አስኪያጅ
____________________________________________________________________________________________________

השותפים

השותפים שלנו

  • קרן עזריאלי

    קרן עזריאלי

  • משרד הבריאות

    משרד הבריאות

  • הקרן לידידות

    הקרן לידידות

  • משרד הקליטה

    משרד הקליטה

  • שרותי בריאות כללית

    שרותי בריאות כללית

  • לאומית שירותי בריאות

    לאומית שירותי בריאות

  • סאנופי

    סאנופי

  • pfizer

    pfizer

  • הסוכנות היהודית לארץ ישראל

    הסוכנות היהודית לארץ ישראל

  • שתיל

    שתיל

  • אוהלי רחמים

    אוהלי רחמים

  • Kathryn Ames Foundation

    Kathryn Ames Foundation

  • Orion

    Orion

  • The Levin Family

    The Levin Family

  • הרשויות המקומיות

    הרשויות המקומיות

צרו קשר

Please type your full name.
Invalid email address.
Invalid Input
Invalid Input
אתר זה מוגן על ידי reCAPTCHA ו-Google מדיניות הפרטיות וכן תנאים והגבלות חלים.
Handsrtl