קורונה

קורונה

የኮሮና ቫይረስ በዚህ በቤተስብ ስሙ ይጠራ እንጅ በውስጡ ልዩ ልዩ ዝርያዎችን የያዘና ከላይኛው መተንፈሻ አካል ጀምሮ ወደታች በመውረድ በሳንባ ላይ ከፍ ያለ በሽታን በማባባስ የሚጎዳና እስከ ሞት አደጋም የሚያድርስ ነው ። ቫይረሱ ስሙን ያገኘው ከአካሉ ቅርጽ ነው ፤ ይህም ማለት በላቲን ቋንቋ " ኮሮና " ማለት " ሆሎ " ወይንም " ክራውን - ዘውድ " ማለት ሲሆን፣ የቫይረሱ ውጫዊ አካል የዘውድ ቅርጽ እንዳለው መስሎ ስለሚታይ ነው ።የኮሮና ቫይረስ እስከ አሁን ቢያስ ሶስት ታዋቂ ዝርያቶች አሉት ፦
1ኛ . የመካከለኛው ምሥራቅ የመተንፈሻ አካል ሕመም መነሻ ፤ሜርስ ( MERS-COV)
2ኛ . የከባድና የአጣዳፊ የመተንፈሻ አካል ሕመም መነሻ ፤ ሳርስ (SARS-COV)
3ኛ . የዛሬው የአዲሱ ወረርሽኝ በሽታ መነሻ ናቸው ፤ ኮሮና (CR-COV)
ይህ ቫይረስ የሚያጠቃው በዋናነት የመተንፈሻ አካልን (ጉሮሮን ፤ ሳንባን ) ነው ። በተነጻጻሪነት ሲወዳደር ፣ ይህ ቫይረስ መጠኑ ትልቅ፣ ጠባዩ በሞቃት የአየር ጠባይ በቀላሉ የሚጠቃ ፤ ተላላፊነቱ በሳልና በንጥሻ ጠብታዎችና እጅ ለእጅ የመጨባበጥ ሁኔታ ዋና መንገዶች ናቸው ።
ዛሬ " በዋላ " የኢሪንተርኔት የዜና አውታር በተገለጠው መሠርት በዓለም ላይ ያለበት የስርጭት
ሁኔታ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ይመስላል፦
አድራሻ የታመሙ ሰዎች የሞቱ ሰዎች የዳኑ ሰዎች በአጠቃላይ ገዳይነቱ በ% ሲሰላ
በዓለም ውስጥ 126,358 4,638 68,284 2.72% (ይህ መጠን ከአገር ወደ አገር በጣም ይለያል)
በእስራኤል ውስጥ 100 0 4 0%
አስተያየት፦ እስራኤል እያደረገች ካለው በሽታውን የመከላከል ጥረት አንጻር፣ ሁኔታው በዚህ
ደረጃ ላይ ይገኝ እንጅ ፣ይህን አህዛዊ (የቁጥር) መረጃ በመመልከት ብቻ ሕዝቡ
በመከላከሉ ጉዳይ ላይ ጥረቱ የላቀ መሆን እንዳለበት መዘነጋት የለበትም !!
የኮሮና ቫይረስ በሽታ ዋና ምልክቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎች
በሽታው በአጠቃላይ እንደሌሎች የቫይረስ ሕመሞች ማለትም እንደ ኢንፍሊዊአንዛ / ሻፓአት
ሊመስል ይችላል። ነገር ግን የጉሮሮ መከርከር፣ደረቅ ሳልና ከፍተኛ የሰውነት ሙቅት ዋና
ምልክቶቹ ናቸው። ይህን መሳይ የሕመም ስሜት ሲደርስብን፣ በአፋጣኝ ወደ ማጌን ዳቪድ
101 ስልክ በመደወል አፋጣኝ መመሪያ መቀበል አለብን።
በሽታውን ለመከላከል የሚደረጉ ቀዳሚ የጥንቃቄ እርምጃዎች
 እጅን በሳሙና በመቀባት፣ ከ30-40 ሴኮንድ ለሚሆን ጊዜ አሽቶ መታጠብ (ከምግብ
በፊትና በኋላ፣ ከሥራ በኋላ፣እንግዳ ነገርን ከነካን፣ ከመጸዳጃ ቤት ስንወጣ፣ ምዙዛ
ስንስም፣ ማንኛውንም ሁሉም የተጠቀመበትን የሚጠረጠር ነገር ስንነካ ወይም
ስንጠቀምበት፣ እጅን በንቃት መታጠብ ወይም በአልኮል በተነከሩ ማጽጃዎች ወይም
በልዩ ልዩ ማጽጃ ፈሳሾች(ጀሎች) በመጠቀም መከላከል፣
 አፍና አፍንጫን፣ዓይንን ጨምሮ እንደተለመደው ከመነካካት መታገስ፣
 ጥርጣሬ ባለበት የስብሰባ ቦታ በአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ( ማስክ ) መጠቀም፣
 ስንስልና ስናንነጥስ በእጃችን ውስጣዊ መዳፍ ሳይሆን፣በክርናችን መገደብ ፣ወይም
አፍና አፍንጫን መሸፈን፣
 እጅ ለእጅ የመጨባበጥንና የመሳሳምን ልምድ ለጊዜው መገደብ፣ የሚሉት አስፈላጊ
እርምጃዎች ናቸው።
በሽታው በብዛት የሚያጠቃው ማንን ነው ?
በአጠቃላይ ወረርሽኙ በሽታ ሁሉንም የዕድሜ ክልል ያጠቃል ። ይሁን እንጅ እስከ አሁን
ከተገኘው ኢፒዴሚዎሎጅያዊ መረጃ መሠረት፣ በሽታው በይበልጥ የሚያጠቃው ስር የሰደድ
በሽታ ያላቸውን ሰዎች ነው። ለምሳሌ፣ የስኳር ብዛት በሽታ ፤ ከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ ፤
የልብ በሽታ፣ የመተንፈሻ አክል በሽታና የተፈጥሮ መከላከያ ኋይላቸው ደካማ የሆኑትን
እንደሆነ ታውቋል። ይህም ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑትን አረጋውያንንም ጨምሮ
ነው ። ለጊዜው ከዘጠኝ ዓመት በታች ባሉ ሕጻናት ችግሩ አልታየም ። (የመረጃው ምንጭ ፦
በቅርቡ በቻይና አገር ከ87,000 በላይ በተበከሉ ሰዎች ላይ የተደረገ ሳይናሳዊ ጥናት ከቀረበው
ሪፖርት)፣
ስለዚህ የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የእያንዳንዱ ግለሰብ የግል ኋላፊነቱን በጽኑ መወጣት
አስፈላጊ መሆኑ አያጠያይቅም ። በሽታውን ስለመከላከልና በሽታውን ላለማስተላለፍ ከፍ ያለ
የነቃና እምነት ያለው ኃላፊነት ሊኖረን ይገባል ። ይህ ትግል የአገርን ሉዋላዊነት ከወራሪ ጠላት
እንደመጠበቅ የሚመስል ክቡር ትግል መሆኑን ሰፋ አድርጎ መገንዘብ ግድ ይለናል ። ከ 60
ዓመት በላይ ያለውን ሕዝብና ሕጻናትን በልዩ ትኩረት ማገዝና መንከባከብም ያስፈልጋል ።
የበሽታውን ስርጭት በመከላከሉ ጥረት ላይ እየተሰጠ ስላለው መመሪያ
የወረርሽኙን መዛመት ለመገደብ ይቻል ዘንድ በግለሰብ ደረጃ ፤ በሕብረተሰብ ደረጃና በአገር
አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ መርሆና እርምጃዎችን በጥምረት መሥራት ዋና ጉዳይ ነው ። ስለሆነም
የችግሩን አሳሳቢነት በጥብቅ በመገንዘብ የእስራኤል የጤና ጥበቃ ሚ/ር ከከፍተኛ የጤና
ባለሙያዎች ጋር በመመካከር መመሪያዎችን በማውጣትና በሽታውን በመከላከል ከፍተኛ ጥረት
በማድረግ ላይ ይገኛል ።
ክቡር የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያሚን ናታንያሁ ፤ የጤና ጥበቃ ሚ/ር ሀራቭ ሊጽማንና
የማጌን ዳቪድ አዶም ዋና ሥራ አስኪያጅ ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ ከፍተኛ ውሳኔዎች
ተደርገዋል ። ይኸውም ፦
1ኛ / በሽታው ከተሰራጨባቸው አገሮች ወደ እስራኤል የሚገቡ ሁሉ ለ14 ቀናት በመገለል
ጥበቃ ውስጥ እንዲገቡ ፤
2ኛ / የግል ንጽህና አጠባበቅ ላይ እጅግ ከፍ ያለ ትኩረትና አፈጻጸም እንዲደረግ ፤
3ኛ / የእጅ መጨባበጥ ልምድ ለጊዜው እንዲቆም የሚሉት አብይ ጉዳዮች ናቸው ፣በማለት
መዓሪቭ ጋዜጣ በ4.3. 2020 ባወጣው እትሙ ገልጧል።

השותפים

השותפים שלנו

  • קרן עזריאלי

    קרן עזריאלי

  • משרד הבריאות

    משרד הבריאות

  • הקרן לידידות

    הקרן לידידות

  • משרד הקליטה

    משרד הקליטה

  • שרותי בריאות כללית

    שרותי בריאות כללית

  • לאומית שירותי בריאות

    לאומית שירותי בריאות

  • סאנופי

    סאנופי

  • pfizer

    pfizer

  • הסוכנות היהודית לארץ ישראל

    הסוכנות היהודית לארץ ישראל

  • שתיל

    שתיל

  • אוהלי רחמים

    אוהלי רחמים

  • Kathryn Ames Foundation

    Kathryn Ames Foundation

  • Orion

    Orion

  • The Levin Family

    The Levin Family

  • הרשויות המקומיות

    הרשויות המקומיות

צרו קשר

Please type your full name.
Invalid email address.
Invalid Input
Invalid Input
אתר זה מוגן על ידי reCAPTCHA ו-Google מדיניות הפרטיות וכן תנאים והגבלות חלים.
Handsrtl