25 מרץ 2020
כ"ט באדר, התש"פ
סימוכין 167386320
הודעה לעיתונות
הודעה משותפת – משרד ראש הממשלה ומשרד הבריאות
ጋዜጣዊ መግለጫ
የጠቅላይ ሚኒስት እና የጤና ጥበቃ መ/ቤቶች በጥምር የሰጡት መገለጫ ፤
በእስራኤል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለማቆም የህብረተሰቡ ከቦታ ወደ ቦታ እንቅስቃሴ ለመቀነስ ከዛሬ ሌሊት ጀምሮ መንግስት አዳዲስ መመሪያዎችን በይፋ አፅድቋል::
እነዚህ አዳዲስ መመሪያዎች ከዚህ በፊት ከወጡት መመሪያዎች በተጨማሪ የሕዝብ መናሃሪያ ወደ ሆኑ ቦታዎች መውጣትን ይከለክላል::: በተጨማሪም በጣም አስፈላጊ ያልሆኑ ሱቆች እንዲዘጉና ካልተዘጉ ደግሞ በሥራ ሃላፊዎች ላይ ኃላፊነቱን ይጥላል፤ እንዲሁም የሕዝብ መጓጓዣ ትራንስፖርት መቀነስን ያጠቃልላል ።
እነዚህ አዳዲስ መመሪያዎች ተግባራዊ የሚሆኑት ስራ ዛሬ እሮብ 25/03/2020 ከ17፡00ሰዓት ጀምሮ ሲሆን ፤ ለ 7 ቀናት ይቆያል ።
በተሰጡት የአስቸኳይ ጊዜ አዲስ መመሪያዎች መሰረት ፤ ከምንኖርበት ቋሚ መኖሪያ ቤት ወደ የሕዝብ መናሃሪያ ቦታዎች መውጣት የሚቻለው ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መሪያዎች መንገድ ብቻ ይሆናል ።
- መመሪያ መሰረት ወደ ሥራ ቦታ መሄድ ይቻላል::
- ምግብ ለመግዛት፣መደኃኒቶችና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለመግዛት እንዲሁም ። የተለያዩ እስፈላጊና መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎቶች ለመቀበል መውጣታ ይቻላል::
- የሕክምና አገልግሎት ለመቀበል ።
- የደም ልገሳ ለማድረግ ።
- የፍርድ ቤት ሂደቶችን ለማስፈጸም ።
- የሰልፍ አድማ ለማድረግ ።
- ወደ ክኔሴት ለመሄድ ።
- በማሕበራዊ መስሪያ ቤት አማካኝነት የተለያዩ እንክብካቤዎችን ለመቀበል ።
- አንድ ሰው ወይም በአንድ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ከ100 ሜትር ከቤታቸው ሳይርቁ ለጥቂት ጊዜ መውጣት ይችላሉ ።
- ለሌላ ሰው የሕክምና እርዳታ ለመስጠት ወይም ሌላ ከባድ የሆነና እርዳታ የሚያስፈልገው ችግር ላጋጠመው ሰው እርዳታ ለማቅረብ።
- ፀሎት ማካሄድ የሚቻለው ክፍት በሆነ ቦታ ብቻ ነው ፤ የቀብር ሥነ-ስርዓት ፤ ሠርግ ፤ የግርዛት ሥነ-ስራዓት ፤ በተጨማሪም ፤ አንዲት ሴት ንፁህ ለመሆን ወደ ውሃ መታጠቢያ ገንዳ (ሚቅቬ) መሄድ የምትችለው አስቀድማ መምጣቷን ካስታወቀች በኋላ ብቻ ነው ።
- ለሕብረተሰቡ በጣም አስፈላጊ በሆኑ የሥራ ዘርፍ የሚሰሩ ሰራተኞች ህፃናት ልጆቻቸውን የልዩ ትምህርት ቤት መውሰድ ይችላሉ (የሕብረተሰቡን የጤንነት ጉዳይ በሚመለከትው ትእዛዝ(ህግ) መሰረት ይሆናል)።
- ዎላጆቹ ተለያይተው የሚኖሩ ትስሽ ልጅን ከአንዱ ወላጅ ቤት ወደ ሌላው ወላጅ ማስተላለፍ ይቻላል።
- አንድ ወላጅ በጣም አስፈላጊ ለሆነ ነገር መውጣት ግድ ከሆነበትና ትንሹ ሕጻን ልጅ ከቤት የሚጠብቀው ከሌለ ፤ ሕጽኑን ከቦታ ወደ ቦታ ማዘዋውር ይፈቀዳል ።
በተጭማሪም ፤ የጤና ጥበቃ መ/ቤት በሰጠው መመሪያ መሰረት ፤ የሕዝብ የመንገድ መጓጓዣ ትራንፖትን እስከ 25% መቀነስ ይቀንሳል ።
ሌላው ፤ በታክሲ መጓጓዝ የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ሲሆን ፤ ለሕክምና መቀበል ለሚሄድ ሰው ደግሞ አብሮት የሚሄድ ተጨማሪ ተሳፋሪ አብሮት እንዲሳፈር ሲፈቀድ ፤ 2 ተሳፋሪዎቹ የሚቀመጡት ከኋለኛው ቦታና መስኮቶቹ ክፍት መሆን አለባቸው ።
ይህ አዲስ መመሪያ በተጨማሪ እንደሚገልፀው ከሆነ ፤ በማንኛውም የሕዝብ መናሃሪያ ቦታዎችና የሥራ ቦታዎች አንድ ሰው ከሌላኛ ሰው የ 2 ሜትር እርቀት መጠበቅ አለበት ፤ በጣም አስፈላጊ ለሆኑ የመኪና መጓጓዞች ደግሞ 2 ተሳፋሪዎች ብቻ መሆን አለባቸው ፤ ሰራተኞችን ከቤት ወደ ሥራ ቦታ የሚያመላልሱ መኪናዎች ስራቸውን መስራት ይቀጥላሉ በዚህ ዙሪያ በተሰጡት መመሪያዎች መሰረት ።
በተጨማሪም ፤ ማንኛውም የሥራው ኃላፊው ሰራተኞቹን ወደ ሥራ ቦታ ሲገቡ የሰውነት ሙቀታቸውን የመለካት የግዴታ አለበት ሙቀት ከ38 ፄልዚዉስ በላይ የሆነ ሰራተኛ ወደ ሥራ ቦታ መግባት የተከለከለ ነው ።
ከዚህ ጎን ለጎን ፤ የተለያዩ የምግብ ተላላኪዎች ፤ የተለያዩ ጋዜጦችና በጣም አስፈላጊ የሆኑ የቤት ጥገና ሥራዎች መስራት ይቀጥላሉ ፤ እንደ ፤ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣የመገናኛ ዓውታሮች መሳሪያዎችና አገልግሎቶች እንዲሁም የሕክምና መሳሪያዎች በተላላኪዎች አማካኝነት አገልግሎቱን ይቀጥላሉ፤ በኢንተርኔት የሚደረጉና እስከ መኖሪያ ቤቶች በተላላኪ የሚላኩ ማንኛውም ሽያጮች የተፈቀዱ ናቸው ፤ በተላላኪ የተላኩት ቁሳቁሶች ተላላኪው ከቤቱ በር ላይ ማስቀመጥ አለበት ።
ከምግብ ቤት ውጭ ምግቦችን ለሚሸጡ ድርጅቶች ደግሞ ፤ መሸጥ የሚችሉት በተላላኪ በኩል ብቻ ነው ፤ የመድኃኒት መደብሮች (ፌርማሲዎች) ፤ የዓይን ምርመራ የሚያደርጉ ድርጅቶች ፤ የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች ወይምቁሳቁሶችን የሚሸጡ ሱቆች ፤ በተሰጠው መመሪያ መሰረት ፤ አንዱ ሰው ከሌላኛው ሰው የ 2 ሜትር ርቀት በመጠበቅና የሰው ስብስብን በመቀነስ ስራቸውን መስራት ይችላሉ ፤ ይህም ማለት ፤ በአንድ የቁሳቁስ ሻጭ ከ4 የክፍያ ቦታ (ኩፓ) ሰው መክፈት የለባቸውም ።
የተሰጡትን አዲስ ትእዛዞችና መመሪያዎች ሳያከብር የተገኘ ግለሰብ ፤ ከባድ ወንጀለኛ እንደሚሆን ማወቅ አለበት ፤ ይህም ማለት ፤ መመሪያውን ለማያከብሩ ሰዎች የተለያዩ የገንዘብ ቅጣት ይሰጣቸዋል ፤ በተጨማሪም ፤ የእስራኤል ፖሊስ እነዚህን መመሪያዎች ለመተግበር ሙሉ ስልጣን እንደተሰጠው መመሪያው ይገልፃ ።
መንግስት ያፀደቃቸው እነዚህ የአስቸኳይ ጊዜ መመሪያዎች በጤና ጥበቃ መ/ቤት አማካኝነት በአስቸኳይ ይሰራጫሉ ።
ከዚህ በላይ ከተገለፁት መመሪያዎች ውጭ፤ የቫይረሱን መዛመት ለማቆም ፤ የተሰጡትን መመሪያዎች ባንድ ላይ ማክበርና መፈጸ በጣን አስፈላጊ ነው ፤ ከ60 ዓመት እድሜ በላይ ላሉ ሰዎች እና በአደጋ ላይ የሚገኙ ሁሉ ወደ ሕዝባዊ መናህሪያ መንገዶች አለመውጣትና ከቤታቸው መቀመጥ አለባቸው ።
ኢያል ባሶን
የጤና ጥበቃ መ/ቤት ቃል አቀባይ